top of page
ስለ ሬማ እምነት
በዩኬ ውስጥ በሬማ እምነት አገልግሎት የተተከሉ አብያተ ክርስቲያናት
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደሙ ተቤዥቶ የወለዳት ወደ ራሱ የጠራት ደግሞም ራስ የሆነላት የገሃንም (የሲኦል) ደጆች የሆኑት ሞትና መውጊያው የማይቋቋሟት ዓለሙን ከእግዚአብሔር ጋር የማስታረቅ አገልግሎት የተሰጣት በእግዚአብሔር ሀይልና ሥልጣን ጸጋ የተሞላች በምድር የምትሰራ የክርስቶስ አካል ናት (ኤፌሶን 1፣15-23)
በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተዋጅተን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን በሞቱና በትንሳኤው እናምናለን።
መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል እና ለሰው ልጆች ያለው መለኮታዊ ፈቃድ እና ሥርዓት አድርገን እንቀበላለን፣
ቤተ ክርስቲያን ዳግመኛ የተወለዱት አንድ እምነት ያላቸው ቅዱሳን ለአምልኮ፣ ለጸሎት፣ ቃሉን ለማጥናት እና ላልሰሙት የምሥራቹን የሚሰብኩበት ቦታ ነው።
እርስ በርሳችን ለመታነጽ እና ለመካፈልም የጸጋ ስጦታዎችን የምንካፈልበት ጉባኤ ነው.. የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያዝነው የእግዚአብሔር እርሻና ሕንፃ ነን።
እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ራዕይ እንከተል
እግዚአብሔርን የማገልገል ተልእኳችንን ይቀላቀሉን።

bottom of page