top of page
Bible

የወንጌል ስርጭት

Evangelism

የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ዋና ተልዕኮ፡ በማር 16-15" እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።" በማቴዎስ 28፥19-20 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ  እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ” በሚሉት  ትዕዛዛት ላይ የተመሰረተ ነው።

 

ሰብከታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ሆኖ የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በመስቀልም  ስለ ኃጢአተኞች ቤዛነት እንደሞተ በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንተነሣና ጌታም ክርስቶስም ሆኖ ወደ ሰማይ ያረገ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ዳግመኛ በሙታን በሕያዋን ሊፈርድ በክብር በጌትነት እንደሚመጣ  በመስበክና በማስተማር  አማኞችን ወደ አገልግሎታችን የወንጌል ስርጭት ማሰማራት

 

የአገልግሎት ድርሻ

ዋና ተልዕኮውን ግብ ላይ ለማድረስ የሚከተሉትን ዓላማዎች እና የትኩረት አቅጣጫዎች ይከተላል፣ ይተገብራል፣  ያልዳኑ ነፍሳትን በወንጌል መድረስና እንዲድኑ ማገዝ፣ የግለሰብ፣ የቡድን ወይንም የህብረት ምሥክርነት አማራጮችን መጠቀም፣  አባላትን ለወንጌል ሥርጭት ማበረታታትና ማነሳሳት፣  ከቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ጋር በመተባበር አዳዲስ ነፍሳትን የድነትና የደቀ መዝሙርነት ትምህርት እንዲወስዱ  ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣  የወንጌል ስርጭት በየሁለት ሳምንቱ አንድ ጊዜ በለንደንመንገዶች የምሥክርነት ስራውን ያከናውናል።


ምንም እንኳን እያንዳንዱ ክርስቲያን በግለሰብ ደረጃ በየዕለተ ኑሮው ወንጌልን የመመስከር ኃላፊነት ቢኖረውም፣ ይህ የአገልግሎት ክፍል ሌሎች የአገልግሎት ክፍሎችንና የቤተ ክርስቲያንን አባላት በማነሳሳት፣ ለየት ያሉ ቀናቶችን በማቀድ፣  የምሥክርነትና የወንጌል ሥርጭት እንቅስቃሴዎችን ከተማ ዉስጥ ያካሂዳል።  በተጨማሪም የአገልግሎት ዘርፉ ከሚመለከታቸው የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት አቻ አገልግሎት ክፍሎች ጋር በመሆን ወንጌልን ለመመስከርና ለማሰራጨት ይተጋል

ስለ አገልግሎቶቻችን የበለጠ ለማወቅ

እናመሰግናለን

© R H E M A   F A I T H   M I N I S T R I E

bottom of page